ልምድ ልውውጥ በማካሄድ ፣ ምርጥ ተሞክሮዎች በማስፍት የተቋም ግንባታ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን !!
#ኮልፌ_ወረዳ_11_ፓርቲ ሚዲያ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍጸ/ቤት አመራሮች በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 11 በመገኝት የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።
ልምድ ልውውጡ በወረዳው አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ፣ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር የተሰሩ የቢሮ እና የምድረ ጊቢ የማስዋብ ስራዎች፣ አገልግሎትን ለማዘመን የተሰሩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን እና በወረዳ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ያካተተ ነው።
አቶ ሁሴን ቢሉ የወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሀላፊ በወረዳው የተከናወኑ ስራዎችንተግባራቱም በክፍለ ከተማው ድጋፍ፣ በወረዳው አጠቃላይ አመራር እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በወረዳው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የደረሰው ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ምድረ ግቢ ግንባታ ፣አጠቃላይ የሪፎርም ተግባራትን እና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዴት እያከናወኑ እንደሚገኙና ለየት ያሉ የአሰራር ሂደቶችን የሚያሳይ ተግባራት በመስክ ምልከታ ጭምር ልምድ ልውውጥ ተደርጓ
ልምድ ልውውጦች እርሰ በርስ ለመማማር እና የተሻሉ ውጤቶች ለማስመዝገብ ትልቅ ድርሻ አላቸው
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ክፍለ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት ልምድ ልውውጥ አደረገ።
በልምድ ልውውጡም የወረዳው ፓርቲ ኮሚቴ አመራሮች፣ በተገኙበት ከአባላት ምልመላ፤ ወርሃዊ መዋጮ፤ ህገ-ደምብ ውይይት፣ ቢሮ ማዘመን፣ የቤተሰብ ዉይይት፣ የመረጃ አያያዝ ከማዘመን፣ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት፣ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ስራዎች እና ሌሎች የዉስጠ ፓርቲ ስራዎች ያላቸውን ጥሩ ተሞክሮ የጋራ ልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሌክሳንደር ዝናቡ ልምድ ልውውጦች እርሰ በርስ ለመማማር እና የተሻሉ ውጤቶች ለማስመዝገብ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ገልፀዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባዉ ምህረት የፓርቲ ስራዎች ከተግባር አፈጻጸም ጋር በማናበብና በማስተሳሰር የፕሮጀክት እና የልማት ስራዎችን በተግባቦት በመስራት ውጤታማ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ልምድ የሚወሰድባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሰኔ 13/2017ዓ.ም ወረዳ 11 ፓርቲ ሚዲያ
የቀጣይ 90 ቀናት የንቅናቄ ተግባራት ዕቅድ ዉይይት አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት ተካሄደ።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጠቃላይ አመራር በተገኙበት የቀጣይ የክረምት 3ኛ ዙር የ90 ቀናት የንቅናቄ ስራዎች እቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
ይህ ተግባር ካለንበት ሰኔ ወር እስከ ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚከናወን ሲሆን ተግባራቱ በዋናነት በስራ እድል ፈጠራ እና በሌማት ቱሩፋት ስራዎች ያካተተ ነው።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው ምህረት እንደገለፁት በእቅዱ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ የንቅናቄ ተግባራቱ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት ስናከናውናቸው የነበሩ መሆኑን እና በቀጣይ የንቅናቄ ስራውን በዉጤት ልናከናውን ይገባል ብለዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ቶፊቅ በድሩ እንደገለጹት ወረዳችን በዉጤት የታጀበ የተግባር አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዉ ይህን ንቅናቄ ዉጤታማ ለማድረግ የ90 ቀናት የሶስት ወራት እቅድ በማዘጋጀት እና የጋራ በማድረግ ወደ ስራ ሊገቡ እንደሚገባ ጠቁመው በተለይ ከስራ እድል ፈጠራ አንፃር ከ650 በላይ ወጣቶች እና ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የታቀደ መሆኑን ገልፀው ይህንንም ተግባር ለማሳካት ሁሉም የአስተግባሪ ተቋማትና ሴክተር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም በብሎክ ደረጃ የተሸነሸነ እቅድ ቀርቧል፤ በቀጣይም በተቀመጠው መረሀ ግብር መሰረት በሁሉም ብሎኮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶቾ እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በመጨረሻም አመራሩ የህብረተሰቡን ጥያቄ በሚመልስ ሁኔታ በልዩ ትኩረት በመንግስት ታቅደው እየተተገበሩ ያሉ ተግባሮችን አስተሳስሮ በመስራት የታቀደውን እቅድ ማሳካት እንደሚገባ ተገልጿል።
ሰኔ 12/2017 ዓ.ም ኮልፌ ወረዳ 11 ፓርቲ ሚዲያ
በሞዴል ተቋማት ግንባታ እና በፓርቲ ፋይናንስ ዙሪያ ለአዳዲስ አባላት ስልጠና ተሰጠ !!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በአደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪነት ለአዳዲስ አባላት በሞዴል ተቋማት ግንባታ እና በፓርቲ ፋይናንስ አሰራር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።
መርሀ ግብሩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ወርቅነህ ሞርካ ሞዴል የብልጽግና ህብረት በሞዴል ተቋማት ግንባታ እና በፋይናንስ አሰራር ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ካሉ በኃላ የአዳዲስ አባሉን አቅም ማሳደግ የብልፅግናን እሳቤ ለማስረፅ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው የብልፅግና ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን በመግለፅ ለዚህም የፓርቲው አዳዲስ አባላት ተግባሩን ውጤታማ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ አሸናፊ ብርሃኑ የክፍለ ከተማ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን በስልጠናው የሞዴል ተቃማት ግንባታ ለመፍጠር የሚያስፈልጉ በርካታ ነጥቦችን በማንሳት አዳዲስ አባላት በትኩረት በማሳወቅ በቀጣይም በዳበረ አቅም ሁለንተናዊ ተሳትፎአቸውን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ሙሉ ደስታ የክፍለ ከተማ የሰው ሀብትና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ እንደገለፁት ጠንካራ የተደራጀ በአሰራርና መመሪያ የሚመራ የፓርቲ ፋይናንስ የገቢ አሰራር ስርዓት በመከተል የፓርቲውን የፋይናንስ አቅም ማሳደግ ከዘርፉ የሚጠበቅ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የፓርቲ ፋይናንስ አሠራር ላይ የተቀመጡ ዋና ዋና ጉዳዮች በተገቢ ግንዛቤ ተይዞ አሠራርን የተከተለ ውጤታማ ሥራ መስራት አስፈለጊ ስለሆነ እና የውስጠ ፓርቲ ጥንካሬ እየጎለበተ እንዲሄድ የሀብት ምንጭ መለየት፣ ሀብት ማሰባሰብ፣ የሀብት አሰባሰብ ሆነ አጠቃቀም አሠራር የተከተለ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ነው::
በፋይናንስ አፈፃፀም የሚጣሱ የትኛውም የአሠራር ክፍተቶች እንዳይኖሩ እና የተሻለ፣ የተቀላጠፈ አሠራር መትከል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ::
በመጨረሻም በስልጠናው የተሳተፉ አዳዲስ አባላት የተሰጠው ስልጠና አቅምን ለማሳደግ በጣም አስፈላጊ ነው ብለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ሰኔ 11/2017 ዓ.ም ወረዳ 11ፓርቲ ሚዲያ
አመራሩ የሚሰጡትን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ወደ ተግባር በመቀየር የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት መፈፀም እንደሚገባ ተገለፀ።
በዛሬው እለት የኮልፌ ቀራኒዮ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት ተልዕኮ በብቃት መወጣት በሚል ርዕስ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምሕረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) አመካኝነት ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ አጠቃላይ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራኒዮ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በስልጠናው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ስልጠናው የአመራሩን አቅም በመገንባት እንዲሁም የበለጠ በማነሳሳት የፓርቲው እና መንግስት ተልዕኮዎች በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
አቶ ሙሉጌታ አያይዘውም አመራሩ በዚህ ስልጠና ያገኘውን ተጨማሪ አቅሞ ይዞ ወደ ስራ በመግባት በ90 ቀናት የተቀመጡ ከ18 በላይ ግቦች ወደ ውጤት በመቀየር ስራዎችን በውጤት ማጠናቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በስልጠናው የተገኙት አቶ ዳዊት ምንዳዬ በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ ባደረጉት ንግግር ኮልፌ በ2017 በጀት አመት በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሰጡት ክፍለ ከተሞች ከፊት የሚገኝ መሆኑን በማስታወስ መሰል ስልጠናዎች የአመራሩን የመምራት አቅም የሚጨምሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስልጠናው የሰጡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምሕረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ሲሆኑ ተልዕኮን በአግባቡ መወጣት በሚል ርዕስ ትኩረት የሚፈልጉ ሀላፊነት መውሰድ፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ የህዝብ ፍላጎት መረዳትና ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲሁም ተልእኮን በአግባቡ ለመወጣት ችግር የሚሆኑ በርካታ ፅንሰ ሀሳቦች የመፍትሄ መንገዶች ዙሪያ ዝርዝር ገላፆ አድርገዋል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በመጠየቅ የራሳቸው ሚና እንደሚወጡ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
መደበኛ እና ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት ተገመገመ።
ግንቦት 02/2017 ዓ.ም ኮልፌ ወረዳ 11 ፓርቲ ሚዲያ
የመንግስት እና ፓርቲ ተግባራት የስራ ዕድል ፈጠራ፣የሌማት ትሩፋት፣ የECD፣ የቢሮ ምቹ ሁኔታ፣የሠላም ፀጥታ ስራዎች ሌሎች ወቅታዊ እና መደበኛ የመንግስት እና የውስጠ ፓርቲ ተግባራት ጠቅላላ አመራር በተገኘበት በጋራ ተገምግሟል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁሴን ቢሉ እንደገለፁት ሁሉም አመራር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ስራዎችን በውጤት ማጀብ ተግባራትን በተሻለ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ ገልፀው፤ ተግባራትን በማስተሳሰር ውጤታማ የሆነ ስምሪት ውስጥ መሆን ያስፈልጋል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል:
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው ምህረት በበኩላቸው ተግባራትን አስተሳስሮ በመስራት በክፍተት የተነሱ ተግባራት ላይ በትኩረት በማረም ሁሉንም ተግባራት በውጤት ማጀብ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በትኩረት የተገመገሙ የመንግስትና የፓርቲ እንዲሁም ወቅታዊ ስራዎች አፈፃፀም የታዩ ክፍተቶችን በማረም ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ውጤት ማምጣት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።
"የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሠላም ነው"
በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች
በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት የሚገልፅ ሰልፍ አካሂደዋል።
ነዋሪዎቹ ለትግራይ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነት አያስፈልግም፣ በክልሉ ያለውን ሠላማዊ እንቅሥቃሴ እና መሠል ሥራዎች በማሥተጓጎል የሚገኝ ጥቅም የለም የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ለትግራይ እና ነዋሪዎቿ ሠላም በምንም የማይተካ መሆኑንም ሰልፈኞቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በመነጋገር እንዲፈቱ እና ለሠላም ጠንቅ ከመሆን እንዲታቀቡም አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት፦ የትግራይ ክልል ሕዝብ ካለፈው ቁስሉ ሳያገግም አሁንም በጦርነት ስጋት እና ሽብር ላይ መሆኑን ገልፀው በትግራይ ልህቃን መካከል መከፋፈል መኖሩን በማንሳትም ልህቃኑ ልዩነታቸውን በመግባባትና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ መጠቆማቸው ይታወሳል።
የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በቀጣይ በትኩረት ለመስራት ካስቀመጣቸው ስምንት አንኳር ጉዳዮች ዘላቂ እና አዎንታዊ ሰላምን ማረጋገጥ ነው። ፓርቲው ዘላቂው መንገድ የሰላም መንገድ መሆኑን በፅኑ ስለሚያምን የሰላም አማራጮችን በመጠቀም የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ይሰራል።
የወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ ኮሚቴ መደበኛ እና ወቅታዊ የፓርቲ ተግባራት ላይ አፈፃፀም ገምግሟል ።
የኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 11 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፓርቲ ኮሚቴ የፓርቲ ተግባራት ወቅታዊ አፈፃፀም ዝርዝር ቀርቦ ያሉበትን ደረጃ መገምገም ተችሏል ።
ያሉትን ጥንካሬዎች በተሻለ መንገድ በማስቀጠል በክፍተት የታዩትን ቦታዎች በፍጥነት በማስተካከል በጋራ ውጤት ተኮር የሆኑ ተግባራትን ማስቀጠል የሚገባ መሆኑን የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሳምራዊት እምባዬ ገልፀዋል ።
ጥር 28/2017 ዓ/ም
ከብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የጉባኤ ማጠቃለያ አቅጣጫ እናየአቋም መግለጫ
ባለፉት ሦስት ዓመታት የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግቦችን ለማሳካት ታልመው የተፈጸሙ የፖለቲካና የአደረጃጀት ሥራዎች ፓርቲው፣ ከዕድሜው የቀደመ የውጤትና የዕድገት ምዕራፍ ውስጥ እንዲገኝ መታየቱ ተመላክቷል።
ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብርና በፉክክር መካከል ሚዛን በመጠበቅ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ለመቀየር ያሳየነው ቁርጠኝነትም ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እንደሚሆን አይተናል ሲል ፓርቲው ገልጿል።
ፓርቲው፣ በቅድመ ጉባዔ ኮንፈረንሶች እና በጉባኤ አማካኝነት ባካሄዳቸው ተከታታይ ውይይቶች ጠንካራ፣ ጤነኛና ውጤታማ ፓርቲ የመገንባት አጀንዳ ቋሚ ትግል የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘቡንም አስታውቋል፡፡
የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን በማጎልበት፣ የአደረጃጀቶችን ሁለገብ የተጽዕኖ አድማስ በማስፋት፣ የአሠራር ሥርዓቶችን የበለጠ በማዘመንና የኢንስፔክሽንና የሥነ ምግባር ኮሚሽኖችን በየደረጃው ማጠናከር፤ እንደሚገባም ታምኖበታል ነው ያለው ፓርቲው፡፡
ጉድለቶችና ብልሽቶችን የማረም ዐቅም ያለው፣ ሀገራዊ የመንግሥት ኢንሼቲቮችን በሐሳብ የሚመራና የሕዝብ ንቅናቄዎችን በብቃት የሚያስተባብር ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር የጋራ አቋም መወሰዱንም ገልጿል፡፡
ፓርቲው፣ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታትም የአመራርን እና የአባላትን ብቃትና ጥራት በሥልጠናና በተከታታይ ውይይቶች በማሳደግ በአስተሳሰብና በተግባር ብልጽግና የሆኑ፣ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በውጤታማነት እየፈጸሙ የሕዝቡን ሕይወት የሚለውጡ፣ በሥራና በመኖሪያ አካባቢያቸው የጠንካራ ዲስፕሊንና የመልካም ሥነ ምግባር መገለጫ የሆኑ፣ የኢትዮጵያን ሕልም እውን የሚያደርጉ የለውጡ ሞተር እንዲሆኑ በማድረግ በላቀ ውጤት የሚገለጽ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የሚሰራ መሆኑንም አስታቀዋል፡፡
ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት ውጤታማ የምዘናና የግምገማ ሥርዓት እንዲዘረጋ፤የሥነ ምግባርና የሞራል ዝቅጠት ተጠቂ በሆኑ አመራሮችና አባላት ላይ የማረም ተግባር እንዲከናወን፤አዳዲስ አባላትን የመመልመል ሥራ በጥራትና በብቃት እንደሚሰራም ነው ፓርቲው ያመላከተው፡፡
ይህንን ለማከናወንም ዘመኑን ማላመድ የሚያስችሉ የሐሳብና የታሪክ ውሕደት በመፍጠር፣ መዋቅራዊ ልህቀት በማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ስክነትን እውን በማድረግና የውጤት ዘላቂነትን በቁርጠኝት ለመፈጸም ዳግም ቃል መግባቱንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡
1, "በላቀ ውጤት የሚገለጽ ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግስት እና ሀገረ መንግስት ለመገንባት እንሰራለን!!"
ባለፉት ሦስት ዓመታት የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግቦችን ለማሳካት ታልመው የተፈጸሙ የፖለቲካና የአደረጃጀት ሥራዎች ፓርቲው፣ ከዕድሜው የቀደመ የውጤትና የዕድገት ምዕራፍ ውስጥ እንዲገኝ መታየቱ ተመላክቷል።
ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብርና በፉክክር መካከል ሚዛን በመጠበቅ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ለመቀየር ያሳየነው ቁርጠኝነትም ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እንደሚሆን አይተናል ሲል ፓርቲው ገልጿል።
ፓርቲው፣ በቅድመ ጉባዔ ኮንፈረንሶች እና በጉባኤ አማካኝነት ባካሄዳቸው ተከታታይ ውይይቶች ጠንካራ፣ ጤነኛና ውጤታማ ፓርቲ የመገንባት አጀንዳ ቋሚ ትግል የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘቡንም አስታውቋል፡፡
የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን በማጎልበት፣ የአደረጃጀቶችን ሁለገብ የተጽዕኖ አድማስ በማስፋት፣ የአሠራር ሥርዓቶችን የበለጠ በማዘመንና የኢንስፔክሽንና የሥነ ምግባር ኮሚሽኖችን በየደረጃው ማጠናከር፤ እንደሚገባም ታምኖበታል ነው ያለው ፓርቲው፡፡
ጉድለቶችና ብልሽቶችን የማረም ዐቅም ያለው፣ ሀገራዊ የመንግሥት ኢንሼቲቮችን በሐሳብ የሚመራና የሕዝብ ንቅናቄዎችን በብቃት የሚያስተባብር ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር የጋራ አቋም መወሰዱንም ገልጿል፡፡
ፓርቲው፣ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታትም የአመራርን እና የአባላትን ብቃትና ጥራት በሥልጠናና በተከታታይ ውይይቶች በማሳደግ በአስተሳሰብና በተግባር ብልጽግና የሆኑ፣ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በውጤታማነት እየፈጸሙ የሕዝቡን ሕይወት የሚለውጡ፣ በሥራና በመኖሪያ አካባቢያቸው የጠንካራ ዲስፕሊንና የመልካም ሥነ ምግባር መገለጫ የሆኑ፣ የኢትዮጵያን ሕልም እውን የሚያደርጉ የለውጡ ሞተር እንዲሆኑ በማድረግ በላቀ ውጤት የሚገለጽ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የሚሰራ መሆኑንም አስታቀዋል፡፡
ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት ውጤታማ የምዘናና የግምገማ ሥርዓት እንዲዘረጋ፤የሥነ ምግባርና የሞራል ዝቅጠት ተጠቂ በሆኑ አመራሮችና አባላት ላይ የማረም ተግባር እንዲከናወን፤አዳዲስ አባላትን የመመልመል ሥራ በጥራትና በብቃት እንደሚሰራም ነው ፓርቲው ያመላከተው፡፡
ይህንን ለማከናወንም ዘመኑን ማላመድ የሚያስችሉ የሐሳብና የታሪክ ውሕደት በመፍጠር፣ መዋቅራዊ ልህቀት በማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ስክነትን እውን በማድረግና የውጤት ዘላቂነትን በቁርጠኝት ለመፈጸም ዳግም ቃል መግባቱንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡
2. ጠንካራ የተቋም ግንባታ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት!!
የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሥራውን በጠንካራ መሠረት ላይ ለማቆምና ጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ለመፍጠር በትኩረት እንሰራለን!!
ዴሞክራሲን ተቋማዊና ሕዝባዊ ባህል በማድረግ የሀገረ መንግሥት ቅቡልነትን ለማረጋገጥ ወደ ተጨባጭ ሥራ መገባቱ ተመልክቷል።
የተጀመረውን የተቋማት ሪፎርም በየዘርፉና በየደረጃው አጠናክሮ በማስቀጠልና ነጻ፣ ገለልተኛና ብቃት ያላቸውን ተቋማት በማባዛት የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሥራውን በጠንካራ መሠረት ላይ ለማቆምና ጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ተመልክቷል፡፡
መንግሥት ባለፉት ሦስት ዓመታት ልዩ ልዩ ሀገራዊ የዴሞክራሲ ተቋሞችንና የሀገር ደኅንነትንና ሉዓላዊነትን የሚጠብቁ ተቋማትን ዐቅም፣ ብቃትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባህል ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የሀገርን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የማስጠበቅ አስደናቂ ውጤት ማስመዝገቡን በስኬት ተመልክቷል።
እነዚህ ተቋማት አስተማማኝ የሀገር ጋሻና መከታ ሆነው እንዲገነቡና ነጻነታቸው ተጠብቆ እንዲቀጥል በቂ ድጋፍ እንደሚደረግም ተመልክቷል ፡፡
የሕዝቡን ፍትሕ የማግኘት መብት በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ፣ የፍትሕ ሥርዓቱን የማዘመን፣ ብቁ ባለሞያዎችን የማፍራት፣ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጥ የማስቻል፣ የዳኞች ነጻነትንና የዳኞች ተጠያቂነትን በሚዛን የማረጋገጥ ተግባራት እንዲከናወኑ ለማድረግ በቁርጠኝነት ለመስራት ጉባኤው በመግለጫው አረጋግጧል፡፡
3. ሕልማችን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን እውን በማድረግ የሀገራችንን ብልጽግና ማረጋገጥ ነው!!
ረጅም በማይባል ጊዜ ውስጥ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ የገነባች ሀገር ማየትን በእጅጉ እንሻለን!
ሁለንተናዊ ብልጽግና የተረጋገጠባት እና አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን የበቃች እና ዓለም አቀፋዊ የተጽዕኖ አድማሷ የሰፋ ኢትዮጵያን እውን ማድረግም ህልማችን ነው።
ብልጽግና በመግለጫው፣ በጉባኤያችንም ሆነ በቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንሶቻችን ሕልማችን እውን ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን ለኢትዮጵያ ብልጽግና በላቀ ተነሣሽነትና ቁርጠኝነት መሥራት እንዳለብን ከልብ ተግባብተናል።
ለኢኮኖሚ ብልጽግና ግቦቻችን በጋራ በመቆም ኢኮኖሚያችን ነባር አቅሞችን የሚያጠናክር፣ ወደ አዳዲስ ዘርፎች የሚሸጋገር እና ወደ መጪው ዘመን የፈጠራ ኢኮኖሚ የሚያስፈነጥር እንዲሆን በውጤታማነት ለመታገልም ወስነናል።
ዘላቂ የልማት ፋይናንስ ሥርዓት በመፍጠር፣ ሀገርን ከብድር ጫና የሚያላቅቅ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠናል።
ገቢ የመሰብሰብ አቅምን በማጎልበት የሕዝቡን አዳጊ ፍላጎቶች ለመመለስ በቁርጠኝነት እንሰራለን።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብርን ወደ ቋሚ ሕዝባዊ ባህልነት እንዲሸጋገር የሕዝቡን ተሳትፎ ከፊት ሆኖ ለመምራት ጠንካራ አቋም የወሰድን ሲሆን ፤ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የተቃና የኢኮኖሚ ማእቀፍ በመገንባት ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ተደምሮ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር በማምጣት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ በመፍጠር፣ በመፍጠን እና በማላቅ እንሰራለን፡፡
4. አካታች ማህበራዊ ልማትን ማረጋገጥ፣ ማህበራዊ ብልፅግናን እውን ማድረግ፣
ብልጽግና ማኅበረሰቡ ሁለንተናዊ ደኅንነቱና ክብሩ ተጠብቆለት ማኅበራዊ መስተጋብሩም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ለማስቻል ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ አካታች ማኅበራዊ ልማት ዓላማን ይዞ በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል።
ፓርቲው ጥራት ያለው ትምህርት ለትውልድ ሁለንተናዊ ልህቀት ወሳኝ ግብአት መሆኑን ያምናል፡፡ በሽታን ቀድሞ መከላከልና አክሞ ማዳን ለጤናማና አምራች ትውልድ ግንባታ ያለዉን ፋይዳም ያምናል፡፡
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አነሣሽነት “ትምህርት ለትውልድ” የሚል ፕሮግራም ተቀርጾ በ2016 እና በ2017 ዓ.ም ብቻ 39 ቢሊዮን ብር የሚገመት የሕዝብ ተሳትፎ ለትምህርት ዘርፍ ልማት ውሏል፡፡
አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን እና ይህንኑ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየርም የትውልድ ዕሴት ግንባታ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ትውልዱ መቻቻልን፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን/እኅትማማችነትንና ዐርበኝነትን እየተማረ እንዲያድግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት የሚረዳ ሀገራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ተቀርፆ እንደሚሠራበት ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ መልክ ለጤና ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የጤና መድኅን ተጠቃሚዎችን የማበራከት፣ ሆስፒታሎችንና የጤና ጣቢያዎችን የማስፋፋት ሥራዎችን ጨምሮ አመርቂ የጥራትና የተደራሽነት የማሻሻያ ርምጃዎች መወሰዳቸውንም ማየት ተችሏል።
ፓርቲው ሰው ተኮር ባህሪውን መሠረት በማድረግ የሕጻናትን፣ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ መብት እና ጥቅም የሚያስከብሩ፣ ክብርና ደኅንነት የሚያስጠብቁ፣ ዐቅመ ደካሞችን እና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚደግፉ ሥራዎች በውጤታማነት መከናወናቸው የሚበረታታ ሲሆን ፣ የወጣቶችና ሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያም ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን አይተናል።
ብልፅግና ፓርቲ የተጀመሩ የማኅበራዊ ልማት ሥራዎች የዕድገትና የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ግቦችን በሚያሳካና ማኅበራዊ ብልጽግናን በሚያረጋግጥ መልኩ በከፍተኛ ቁርጠኝነት አጠናክሮ ይቀጥላል!!
5. ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጠናከር አስተሣሣሪ ትርክት የበላይነት ማግኘት አለበት!!
ብልፅግና ፓርቲ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጠናከር እና የሀገረ መንግሥት ግንባታ እንዲሳካ ነጣጣይ ትርክቶች ተሸንፈው አስተሣሣሪ ትርክት የበላይነትን እንዲያገኝ ይሰራል!
ብሔራዊነት ገዥ ትርክት ሆኖ በልሂቃን እና በሕዝቡ ዘንድ እንዲሠርጽና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጠናከር እንደሚሰራ የገለጸው ፓርቲው፣ ይህንንም የበለጠ ለማሳካት በማህበረሰቡ መካከል መግባባትን የሚፈጥሩ ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ውይይቶች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎችና በሁሉም አማራጭ መንገዶች እንደሚከናወኑ አመላክቷል፡፡
ፓርቲው፣ በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ውይይቶችን በማድረግ የብሔራዊነት ገዥ ትርክት እንዲሠርጽና በሕዝቦች መካከል ትሥሥርና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲፈጠርም ይሰራል፡፡
የሚዲያ ነጻነትና ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አፍራሽ ተልዕኮ ይዘው ሚዲያውን ለግጭት፣ ለብጥብጥና ለወንጀል በሚጠቀሙ አካላት ላይ ሕግ የማስከበር ሥራም ይሰራል፡፡
ፓርቲው፣ የብልጽግና አመራሮችና አባላት መላውን ሕዝብ በማሳተፍ፣ ማኅበራዊ ሚዲያውን ለገዥ ትርክት ግንባታ፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ለዕውቀት ሽግግር እና የኢትዮጵያን እውነት ለመግለጥ እንደሚጠቀምበትም ጠቁሟል፡፡
6. ተቋማዊ ባህሪን መሠረት ያደረገ፣ ገቢር ነበብ ሪፎርምን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው!!
ብልጽግና የሀገራችን ሲቪል ሰርቪስ የዕድሜውን ያህል ተቋማዊ ልህቀት ማረጋገጥ አልቻለም ብሎ ያምናል።
በመሆኑም አሁን ላይ የጅምላ ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም እየተደረገ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በየደረጃው እየተተገበረ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ፤ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዐቅም መሪነት የተሣሠረ ፤ ከሌብነት እና ከብልሹ አሠራር የተላቀቀ ፤ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት እንዳለበት ፓርቲው ያምናል።
ለዚህም ተቋማዊ ባህሪን መሠረት ያደረገ፣ ገቢር ነበብ ሪፎርምን ለማሳካት በቁርጠኝነት እና በከፍተኛ ትኩረት እየሠራ ይገኛል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተጀመረው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር በተለያየ መልክና ደረጃ የሚገለጹ ብልሹ አሠራሮች ሕዝባችንን ለእንግልትና ለእሮሮ እያጋለጡ መሆናቸውን 2ኛ ጉባኤው በዝርዝር መገምገሙ ተመልክቷል።
ዜጎች የሚተማመኑበት የፍትሕ ስርዓት ለመገንባት የተጀመረውን የፍትሕ ሥርዓት ሪፎርም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለማሻገር ፓርቲው መወሰኑም ተጠቁሟል።
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙን በፍጥነት በመተግበርም የመንግሥትን የማስፈጸምና የአገልግሎት ዐቅም ለማሻሻልም ጠንካራ ዐቋም መወሰዱ ተመልክቷል።
ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን ለመቆጣጠር በፓርቲው መሪነት በየደረጃውና በየዘርፉ ጠንካራ ትግል ከማካሄድ በተጨማሪ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት እንዲዘረጋ አቅጣጫ ተቀምቷል።
ውጤታማ የሆነ ገቢር ነበብ ሪፎርም ለማካሄድ እና በተለይም የሕዝብ ቅሬታ ምንጭ የሆኑ አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ላይ በልዩ ጥናት የአገልግሎት ማስተካከያ ዘርፎች ለማድረግና የሕዝቡን ርካታ ለማሳደግ ፓርቲው የወሰደውን ጠንካራ አቋም ለማስፈጸም ሌት ተቀን ለመሥራት አባላቱ ቃል ገብተዋል፡፡
7. ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር የዲፕሎማሲ አቅጣጫን በመከተል የፈጸማቸውን ብሔራዊ ጥቅምን ከፍ ያደረጉ ሥራዎችን ሰርቷል!!
ኢትዮጵያን የብሪክስ አባል ለማድረግ የተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግልና የተገኘው ውጤት የፓርቲው እና የመሪው ዘመን የዋጀ ብቃት ህያው ማሳያ እንደሆነ ተመላክቷል።
የዘመናት የትውልድ ጥያቄ የነበረውን ዘላቂ የባሕር በር አጀንዳ በዓለም አደባባይ ተገቢ ትኩረት እንዲሰጠው ከማድረግ በተጨማሪ ጥያቄዉ ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እንዲያገኝ እየተደረገ ያለውን ጥረትም በከፍተኛ አድናቆት ተመላክቷል።
ፓርቲው የቀረፃቸው የዜጐች ክብር የውጪ ግንኙነት መርሕ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎችን ደኅንነት እና ክብር በማስጠበቅ ረገድ ያስገኘው ጥቅምም በሚገባ ተገምግሟል።
ዲፕሎማሲውን ከመሽኮርመም ወጥቶ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት መርሕንና እውነትን መሠረት ባደረገ ይገባኛል ባይነት መጠየቅ እና ማስፈጸም የሚያስችሉ ተጨማሪ አቅጣጫዎችን በመመርመር ትክክለኛ መንገድ መቀየሱም ተመላክቷል።
በመሆኑም እነዚህ አቅጣጫዎች በብቃት እንዲፈጸሙና ዘላቂ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ እስኪያገኝ በሙሉ አቅሙ በተገኘው የዓለም መድረክ ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ቆርጦ እንደተነሳም ፓርቲው አረጋግጧል፡፡
8. ዘላቂ እና አዎንታዊ ሰላምን ማረጋገጥ!!
የሀገር ደህንነትና ሉዓላዊነትን የሚጠብቁ ተቋማት የሀገር ጋሻና መከታ ሆነው እንዲዘልቁ የሀገራዊ ተቋማት ግንባታ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
"ቃላችንን ባህል እናደርጋለን እኔ ለሀገሬ የሠላም ዘብ ነኝ"
የኮልፌ ወረዳ 11 ህዝባዊ ሠራዊት
*********************************
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ "ህዝባዊ ሰራዊት ፥ቃላችንን ባህል እናደርጋለን፥ እኔ ለሀገሬ የሠላም ዘብ ነኝ"በሚል መሪ ቃል ለህዝባዊ የሠላም ሠራዊት የእውቅና ፕሮግራም በወረዳ 11 አስተዳደር ተደረገ።
በፕሮግራሙ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበባው ምህረት አጭር ንግግር አድርገው የእለቱ የክብር እንግዳ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ጋብዘዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ሞርካ እንደገለፁት ፤ዛሬም እንደ ትላንቱ በህብረት ቆመን ጠላቶቻችንን ድል ከመንሳት እና ታሪክ ከመስራት የሚያግደን አንዳች ኃይል የለም!በማለት
የጥምቀት በዓል በሠላምና በድምቀት እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላትን በየደረጃው አመስግነዋል።
ከዚህ በፊት በርካታ የአደባባይና የሃይማኖት በዓላትን ያለ ምንም የፀጥታ ችግር የተወጣነው በጋራ በመስራት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበሩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የእምነት ተቋማት፣ የፀጥታ ኃይሎች፣ የሠላም ሠራዊት፣ አጎራባች ወረዳዎች፣ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማት የምስጋና ምስክር ወረቀት በመስጠት እና የእራት ግብዣ በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
እንኳን ደስ አላችሁ !
የኮልፌ ወረዳ 11 ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት
እንኳን ደስ አላችሁ !
የኮልፌ ወረዳ 11 ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በ6ወር ተግባር አፈፃፀም በክ/ከተማው ካሉ 11 ወረዳዎች የ3ኛ ደረጃ በመያዝ የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል። በድጋሚ!እንኳን ደሰ አላችሁ ደስ አለን!
ወቅቱን የተረዳ አመራር በመፍጠር የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ ዕውን እናደርጋለን።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር አጠቃላይ አመራር እየተሰሩ ያሉ የመንግስት ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል ።
በወረዳችን እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ስራ ዕድል ፈጠራ እና የሌማት ትሩፉት
በውይይቱም የመደበኛ ስራዎች አፈፃፀም በዝርዝር ተገምግመዋል።
በዚህም የመንግስትና ስራዎች በዋናነት
ስራ ዕድል ፈጠራ እና የሌማት ትሩፉት እየተሰሩ እንደሆነና በቀጣይም እነዚህን ጠንካራ ጎኖች እያስቀጠሉ መሄድ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በተጠቃሚነት ስራ ዕድል እና በሌማት ትሩፋቶች ስራዎች አመራሩ በቀሪ ቀናት በትኩረት እስከታች ድረስ በመስራት የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና ክፍተቶችን ማረም እንዲሁም የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በጥብቅ ዲሲፕሊን መፈፀም ያስፈልጋል ተብሏል።
በመጨረሻም አመራሩ ወቅቱን የዋጀ አመራርነት በመስጠት የነዋሪውን ሁለንተናዊ ተሣትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው ተገልፆ የቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል።
ጥር 18/2017 ዓ.ም
"መርሆቻችን ላይ ጸንተን በመቆም ለወረዳችን ሁለተናዊ ብልፅግና እንተጋለን"
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ ከወረዳ አጠቃላይ አመራር ጋር በጋራ ገምግሟል።
በዚህም ወጣቶችንና ሴቶችን ከስራ እድል ተጠቃሚ ከማድረግ፣ የከተማ ግብር ተግባራት፣የፓርቲ ስራዎች፣ ብሎም ሌሎች በስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች በስፋት በመድረኩ ቀርቧል።
መድረኩን የመሩት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበባው ምህረት
እንደተናገሩት በርካታ ተግባራት ከወረቀት ባለፈ እውን እንዲሆኑ በተደረገው ጥረት የአመራሩ ሚና እጅግ የጎለ ነው ሲሉ ተናግረው እንደ ወረዳ በግማሽ አመት አፈፃፀም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ወራት የማካካሻ እቅድ አውጥተን መንቀሳቀስ ይገባናል ብለዋል።
አክለውም ይህ ተግባር በጊዜ የለኝም ስሜት መጓዝ ካልቻልን ያሰብነው ህልም ላይ መድረስ ከባድ ያደርግብናል ስለዚህ ሁሉም በእኩል ስሜት ተግባራትን ለቅሞ መስራት ይጠበቅበታል በማለት አሳስበዋል።
የወረዳው ም/ስራ/አስ/እና ስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ቶፊቅ በድሩ በበኩላቸው እንደ ስራ ክህሎት ጽ/ቤት በርካታ ስራዎችን መስራት ችለናል ነገር ግን በሚፈለገው ልክ ውጤት ማምጣት አልቻልንም። ስለዚህ ችግሮቻችንን በመለይት ስትራቴጂ ቀይሰን ውጤት ማምጣት አማራጭ የሌለን ጉዳይ ነው ተብለዋል።
በመጨረሻም ሁሉም አመራር በቁጭት ተግባራትን በውጤት ማጀብ እንደሚገባ በማስቀመጥ ስብሰባው ተጠናቋል።
ጥር 15/2017 ዓ.ም
"እግዚአር አብ የጥምቀት ክብረ በዓል በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 11!!"
የእግዚአር አብ የጥምቀት ክብረ በዓል ሀይማኖታዊ እሴት እና ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት በፍፁም ሰላማዊ እንቅስቃሴ በመከበር ላይ ነው።
በአሁኑ ሰዓትም እግዚአር አብ ታቦት ከማደሪያቸው ወጥተው በእልልታ ታጅቦ በድምቀት ወደ በወረዳ 11 አልፈው መንበረ ክብራቸው እየሄዱ ይገኛሉ።
ጥር 13/2017ዓ.ም
አመራሩ የመንግስትና የፓርቲ የ3 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት በጋራ ገመገመ።
==============+++++++=============
የ2017 በጀት ዓመት የ3 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸምን አስመልክቶ በተደረገው ግምገማ የአግልግሎት አሰጣጣችንን ለማሻሻል በቂ ትምህርት አግኝተንበታል ሲሉ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሁሴን ቢሉ ተናገሩ።
በወረዳ አስተዳደሩ በ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት የተከናወኑ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በመመልከት በአገልግሎት አሰጣጥ፤ በስራ እድል፤ በመሰረተ-ልማት፣ በከተማ ግብርና፣ ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣በሰላምና ፀጥታ፤በበጎ ፈቃድ ስራዎች እንዲሁም በውስጠ-ፓርቲ መደበኛ ተግባራት ዙሪያ በትኩረት ተነስቷል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁሴን ቢሉ እንዳሉት ከመጀመሪያ ሩብ አመት አጠቃላይ ክንውን በቂ ትምህርት በመውሰድ፣ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በጽናት በመታገል፣በሚቀጥሉት ዘጠኝ ወራት ተገልጋዮች ምስክር የሚሆኑበት ውጤት ማስመዝገብ አለብን ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም ድክመትና ጥንካሬን ወደ ራስ በመውሰድ፣ የአመራሩን ስምሪትና ቁርጠኝነት በመፈተሽ በግምገማው የተገኘው ውጤት አመርቂ እንደነበር አስምረውበታል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አበባው ምህረት በበኩላቸው የአመራሩን አቅም በመገንባት፤ ውህደቱን በማጠናከር፤የውስጠ-ፓርቲ ስራዎችን በማዘመንና መረጃ በማጥራት እንዲሁም ክፍተት ያለባቸውን ተጠያቂነት በመፍጠር በበጀት አመቱ ስኬቶች መመዝገባቸውን በአጽንኦት አንስተዋል።
የወረዳው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶፊቅ በድሩ ደግሞ በስራ ፈጠራ፣ በመሰረተ-ልማት፣ ገበያውን በማረጋጋት በተጨማሪም አቅመ-ደካሞችን በመርዳት ዘርፈ-ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን በመግለጽ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ የህዝብ ቅሬታዎችን ለማስተካከል በቁርጠኝነት መስራት እንደማገባ ተናግረዋል።
የወረዳ 11 አስተዳደር በሩብ አመቱ የተሰሩትን የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃጸም ግምገማ በድክመትና በጥንካሬ በመለየት እንዲሁም ባለቤት በመስጠት መገምገም ችሏል።
በመጨረሻም የቀጣይ ስራ አቅጣጫ በመስጠት የዕለቱ የሩብ አመት የስራ ግምገማ ተጠናቋል።
ህዳር 07/2017
መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ መደበኛና ወቅታዊ ስራዎች አፈፃፀም ተገመገመ!!!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር በዛሬው ዕለት መደበኛና ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ከጠቅላላ አመራር ጋር የተገመገመ ሲሆን በዚህም የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ ፣ የህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዣ፤ማስ ስፖርት ዙሪያ ከአጠቃላይ አመራር ጋር ውይይት ተደርጓል ።
በፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ተጨባጭ የሆነ ለውጥን ለማምጣት በመደመር እሳቤ የአመራር ሚናችንን በአግባቡ መወጣትና ወቅታዊ የሆኑትን ሁሉንም ተግባራትን በፍጥነት ወደ ተቋም ግንባታ በማሳደግ ለቀጣይ ተልዕኮዎች የተሻለ አቅምን የሚፈጥር እንደሚሆን ማድረግ እንዲሁም ትኩረት የሚሹትን ጉዳዮች ቅድሚያ ሰጥተን ማከናወን ይገባናል ሲሉ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው ምህረት ገልፀዋል ።
በተጨማሪም የወረዳው ም/ስራ አስፈፃሚና ስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ቶፊቅ በድሩ ተግባራት ላይ ውጤታማ አፈፃፀምን ለማስቀጠል ለነገ የማይባል ፈጣን እርምጃ የሚፈልግ በመሆኑ መደበኛ ስራዎችን ከወቅታዊ ተግባራት ጋር አስተሳስሮ በማከናወን በቁርጠኝነት በመስራት ውጤታማነትን የስራችን አካል ማድረግ ይገባናል በማለት ገልፀዋል ። በዚህም ስራ እድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከወቅታዊ ተግባራት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ህዳር 13/2017
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የሰራተኞች እውቅናና ማበረታቻ ፕሮግራም አደረገ።
ሲቪል ሰርቫንቱ እውቅና መስጠት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ ትልቅ ሚና እንዳለው እና የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አድምጦ ምላሽ ለመስጠት ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
በኮልፌ ወረዳ 11 አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2016 በጀት አመት የሰራተኞችና የተቋማት እንዲሁም የልማት ኮሚቴዎችና ሌሎች አደረጃጀቶች የእውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር አካሄዷል። በመርሀ ግብሩ በ2016 በጀት አመት በስኮርካርድ አፈፃፀም ከ95% በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ሰራተኞች የ1000 ብር ቦንድና ሰርተፊኬት ፤ ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተቋማት ለሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ፅ/ቤት ፣ ግንባታ ፈቃድ ፅ/ቤት እና ንግድ ፅ/ቤት የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሲሆኑ በዘርፋቸው ከ1 ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች በልማትና በፀጥታ ስራ ሲሳተፉ ለነበሩ አደረጃጀቶች እውቅና ተሰጥቷል።
አቶ ሁሴን ቢሉ የወረዳ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ በእውቅና መርሀ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በ2016 በጀት አመት ከአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ፣ ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠርና ሌሎች መደበኛና የንቅናቄ ስራዎች በብቃት በመፈፀም እንደ ክ/ከተማም ሆነ እንደ ከተማ እውቅና አግኝተናል ይህ ደግሞ የጋራ የሁላችንም ድምር ውጤት በመሆኑ ዛሬ እናንተን የምናመሰግንበትና እውቅና የምንሰጥበት ቀን ሲሆን የ2016 በጀት አመት አፈፃፀማችንን እንደ መስፈንጠሪያ በመጠቀም በ2017 በጀት አመት እጅግ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ለዚህም ሁሉም ሰራተኛ የአገልጋይነትን ስሜት በመላበስ ህብረተሰቡን ማገልገል ይኖርበታል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ለፐብሊክ ሰርቫንቱ እውቅና መስጠትና ማበረታታት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥና የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አድምጦ ምላሽ ለመስጠት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ሲቪል ሰርቫንቱ በፍፁም ቅንነት ሁሉንም ዜጋ እኩል ማድመጥ ፤ እኩል ምላሽ መስጠትና ፤ እኩል የማገልገልን ባህል ማስቀጠል አለበት ያሉ ሲሆን በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ ስራ በመሆኑ በየብሎኩ ያሉ ስራ ፈላጊዎችን ከመለየት ጀምሮ እስከ ስልጠና ማመቻቸትና ስራ ማስያዝ ድረስ ጠንክረን በመስራት "በሀሳብ ልዕልና ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና" ልንሻገር ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ህዳር 12/2017
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሚገኙ የመስረታዊ ድርጅት አመራሮች የጋራ ውይይት አደረጉ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሚገኙ የመስረታዊ ድርጅት አመራሮች በመደበኛ የግንኙነት ጊዜያቸው ውይይት አደረጉ።
ውይይቱን የመሩት የወረዳ 11 ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበባው ምህረት በውይይት መድረኩ የፓርቲ መሰረታዊ ድርጅት አፈፃፀም በጋራ በመገምገም ያለበትን ደረጃ ለመለየትና የቀጣይ የተግባራትን ስኬታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስን ያለመ ስለመሆኑም ገልጸዋል። በሂደት ጠንካራና ዘመናዊ የክትትልና ድጋፍ ሥርአት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
አክለውም መሠረታዊ ድርጅትን መደገፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረው ህዋሳት ለማጠናከር የመሠረታዊ ድርጅትን ሞዴል አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በቀጣይ መደበኛ የግንኙነት ጊዜ ጠብቀን እየተገናኘን የመጡ ለውጦችን በጋራ እንገመግማለን በማለት ዉይይታቸውን አጠናቀዋል።
ኮልፌ ወረዳ 11 ፓርቲ ሚድያ
ህዳር 11/2017 ዓ.ም
ጽዱ ውብ ምቹ የስራ ቦታ ለሁሉም!
የወረዳ አስተዳደሩን ግቢ የማፅዳት ተግባር
ህዳር 11/2017
ኮልፌ ወረዳ 11 ፓርቲ ሚድያ
የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተሟላ ሁኔታ መመለስ እንደሚገባ ተገለፀ።
በኮልፌ ወረዳ 11 አስተዳደር አጠቃላይ አመራሩ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መነሻ ያደረገ ግምገማዊ ውይይት አካሄደ።
በግምገማዊ ውይይቱ በ1 ኛ ሩብ አመት የተተገበሩ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት እንዲሁም የአመራር ስምሪት የተገመገመ ሲሆን በሩብ አመቱ በጥንካሬ የታዩትን ማስቀጠልና በውስንነት የታዩትን ደግሞ ማረም እንደሚገባ ተጠቁሟል።
አቶ ሁሴን ቢሉ የኮልፌ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተሟላ ሁኔታ መመለስ እንደሚገባና ለዚህም አመራር በቁርጠኝነትመምራት እንዳለበት ገልፀዋል።
አቶ አበባው ምህረት የወረዳ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ እንደገለፁት በ1ኛ ሩብ አመት እንደ መንግስትም እንደ ፓርቲም በርካታ ተግባራትን በብቃት የመራንባቸው እንዳሉ ሁሉ ውስንነቶችን በመለየት በተሻለ ሁኔታ መተግበርና ተግባራትን በውጤት ማጀብ አንደሚገባ ገልፀው በሩብ አመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እንዲቀጥሉና በክፍተት የታዩ እንዲሻሻሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
በተጨማሪም በመድረኩ የስራ እድል ፈጠራ ፣ የህዳሴ ሀብት አሰባሰብ ፣ ጤና መድህንና የሌማት ቱሩፉት መርሀግብር እንዲሁም የ5 ኛ አመት የብልፅግና ፓርቲ ምስረታን ምክንያት በማድረግ እየተሰሩ ያሉ የንቅናቄ ስራዎች ተዳስሰውበታል።
ህዳር 9/2017
Heads of Government Ethiopia
Abiy Ahmed Ali : Abiyi Ahmed Alii; Amharic: ዐቢይ አሕመድ ዐሊ; born 15 August 1976) is an Ethiopian politician serving as the third Prime Minister of Ethiopia since 2018, and as the leader of the Prosperity Party since 2019.[1][2] He was awarded the 2019 Nobel Peace Prize “for his efforts to achieve peace and international cooperation, and in particular for his decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea“..
The president of Ethiopia is the head of state of Ethiopia. The position is largely ceremonial with executive power vested in the Council of Ministers chaired by the prime minister. The current president Taye Atske Selassie Amde (Amharic: ታዬ አጽቀሥላሴ, born 13 January 1956) is an Ethiopian diplomat and politician who is serving as president of Ethiopia since 7 October 2024. He has worked as ambassador on numerous occasions in the United Nations. Prior to assuming this role, he served as the Minister of Foreign Affairs.
Adanech Abebe : Adaanach Abeebee) is an Ethiopian politician and attorney who is serving as the thirty-second mayor of Addis Ababa since 2021. She has been serving as a deputy mayor from 2020 until 2021. She previously was the Minister of Revenue and Customs Authority from 2018[1][2] to 2020, when she became the first female to assume the role of the Federal Attorney General of Ethiopia.[3][4][5][6] She is the first woman to hold the mayorship since it was created in 1910.[
Latest Post
ቃል፣ በተግባር ሰውን ማዕከል ያደረገ ጉዞ ፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽና !!