ፓርቲያችንን በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት !!
Party message Addis Ababa
ወረዳ 11 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው ምህረት
ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 11 በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ካሉት ከ121ዱ ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ነው። እስከ እ.ኤ.አ 2011 ባለው መረጃ መሠረት የሕዝብ ብዛቱ ከ 66000 በላይ ነው።
“የሀሳብ ልዕልና ለሁለተናዊ ብልፅግና”
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
የኮልፌ ወረዳ 11 አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ በወረዳው ኬላ ባጃጅ ተራ አካባቢ የወረዳው ነዋሪ ወጣቶች የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ።
በፅዳት ዘመቻው የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮችና አደረጃጀቶች እንዲሁም የወጣት ሊግና ወጣት ማህበር አባላት ተገኝተውበታል።
ህዳር 10/2017
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሚገኙ የመስረታዊ ድርጅት አመራሮች የጋራ ውይይት አደረጉ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሚገኙ የመስረታዊ ድርጅት አመራሮች በመደበኛ የግንኙነት ጊዜያቸው ውይይት አደረጉ።
ውይይቱን የመሩት የወረዳ 11 ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበባው ምህረት በውይይት መድረኩ የፓርቲ መሰረታዊ ድርጅት አፈፃፀም በጋራ በመገምገም ያለበትን ደረጃ ለመለየትና የቀጣይ የተግባራትን ስኬታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስን ያለመ ስለመሆኑም ገልጸዋል። በሂደት ጠንካራና ዘመናዊ የክትትልና ድጋፍ ሥርአት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
አክለውም መሠረታዊ ድርጅትን መደገፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረው ህዋሳት ለማጠናከር የመሠረታዊ ድርጅትን ሞዴል አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በቀጣይ መደበኛ የግንኙነት ጊዜ ጠብቀን እየተገናኘን የመጡ ለውጦችን በጋራ እንገመግማለን በማለት ዉይይታቸውን አጠናቀዋል።
ኮልፌ ወረዳ 11 ፓርቲ ሚድያ
ህዳር 11/2017 ዓ.ም
መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ መደበኛና ወቅታዊ ስራዎች አፈፃፀም ተገመገመ!!!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር በዛሬው ዕለት መደበኛና ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ከጠቅላላ አመራር ጋር የተገመገመ ሲሆን በዚህም የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ ፣ የህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዣ፤ማስ ስፖርት ዙሪያ ከአጠቃላይ አመራር ጋር ውይይት ተደርጓል ።
በፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ተጨባጭ የሆነ ለውጥን ለማምጣት በመደመር እሳቤ የአመራር ሚናችንን በአግባቡ መወጣትና ወቅታዊ የሆኑትን ሁሉንም ተግባራትን በፍጥነት ወደ ተቋም ግንባታ በማሳደግ ለቀጣይ ተልዕኮዎች የተሻለ አቅምን የሚፈጥር እንደሚሆን ማድረግ እንዲሁም ትኩረት የሚሹትን ጉዳዮች ቅድሚያ ሰጥተን ማከናወን ይገባናል ሲሉ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው ምህረት ገልፀዋል ።
በተጨማሪም የወረዳው ም/ስራ አስፈፃሚና ስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ቶፊቅ በድሩ ተግባራት ላይ ውጤታማ አፈፃፀምን ለማስቀጠል ለነገ የማይባል ፈጣን እርምጃ የሚፈልግ በመሆኑ መደበኛ ስራዎችን ከወቅታዊ ተግባራት ጋር አስተሳስሮ በማከናወን በቁርጠኝነት በመስራት ውጤታማነትን የስራችን አካል ማድረግ ይገባናል በማለት ገልፀዋል ። በዚህም ስራ እድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከወቅታዊ ተግባራት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ህዳር 13/2017
የብልፅና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የፀጥታ አካላት "ህዳር ሲፀዳ" በሚል መሪ ቃል የፀጥታ አካላት የፅዳት ዘመቻ አካሄደ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጽዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ባለሙያዎች የፀጥታ አካላት ፣ የብሎክ አመራሮች በማስተባበር ነዋሪዎችን በማሳተፍ በየቀኑ ብሎክን መሠረት ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ በሦስት ክላስተር ባለሙያው ስምሪት ወስዶ 45 ብሎኮች እንዲፀዱ ማድረግ ተችሏል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው ምህረት አንድነታችንን ከሚከፋፍል ጥላቻ እና ቂም በቀል ወጥተን ወንድማማችነትን በማጠንከር ከቆሻሻ የፀዳች ውብ እና ለነዋሪዎች የተመቸች ከተማ መፍጠር ይጠበቃል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሌላ በኩል በፅዳት ንቅናቄው የተሳተፋ አካላት በፅዳት ዘመቻው የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለነዋሪዎች ምቹ ተስማሚ እና ፅዱ ከተማ ለመፍጠር የቡከላችንን ሚና እንወጣለን በማለት ገልፀዋል።
ማህበረሰቡም ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ህዳር 12 ቀን ህዳር ሲታጠን የሚል ጎጅ ልማዳዊ ድርጊትን በማስወገድ ግቢውንና አካባቢውን በማፅዳት የተፀዳውን ደረቅ ቆሻሻ ለፅዳት ማህበራት በዓይነት በዓይነት በመለዬት እንዲያስረክቡ በስህተት አንዳንድ ግለሰቦች ቆሻሻ ሊያቃጥሉ ስለሚችሉ ማህበረሰቡ በጋራ በመከላከል እንዲያስቆም በመግባባት ተጠናቋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የሰራተኞች እውቅናና ማበረታቻ ፕሮግራም አደረገ።
ሲቪል ሰርቫንቱ እውቅና መስጠት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ ትልቅ ሚና እንዳለው እና የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አድምጦ ምላሽ ለመስጠት ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
በኮልፌ ወረዳ 11 አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2016 በጀት አመት የሰራተኞችና የተቋማት እንዲሁም የልማት ኮሚቴዎችና ሌሎች አደረጃጀቶች የእውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር አካሄዷል። በመርሀ ግብሩ በ2016 በጀት አመት በስኮርካርድ አፈፃፀም ከ95% በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ሰራተኞች የ1000 ብር ቦንድና ሰርተፊኬት ፤ ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተቋማት ለሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ፅ/ቤት ፣ ግንባታ ፈቃድ ፅ/ቤት እና ንግድ ፅ/ቤት የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሲሆኑ በዘርፋቸው ከ1 ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች በልማትና በፀጥታ ስራ ሲሳተፉ ለነበሩ አደረጃጀቶች እውቅና ተሰጥቷል።
አቶ ሁሴን ቢሉ የወረዳ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ በእውቅና መርሀ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በ2016 በጀት አመት ከአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ፣ ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠርና ሌሎች መደበኛና የንቅናቄ ስራዎች በብቃት በመፈፀም እንደ ክ/ከተማም ሆነ እንደ ከተማ እውቅና አግኝተናል ይህ ደግሞ የጋራ የሁላችንም ድምር ውጤት በመሆኑ ዛሬ እናንተን የምናመሰግንበትና እውቅና የምንሰጥበት ቀን ሲሆን የ2016 በጀት አመት አፈፃፀማችንን እንደ መስፈንጠሪያ በመጠቀም በ2017 በጀት አመት እጅግ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ለዚህም ሁሉም ሰራተኛ የአገልጋይነትን ስሜት በመላበስ ህብረተሰቡን ማገልገል ይኖርበታል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ለፐብሊክ ሰርቫንቱ እውቅና መስጠትና ማበረታታት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥና የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አድምጦ ምላሽ ለመስጠት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ሲቪል ሰርቫንቱ በፍፁም ቅንነት ሁሉንም ዜጋ እኩል ማድመጥ ፤ እኩል ምላሽ መስጠትና ፤ እኩል የማገልገልን ባህል ማስቀጠል አለበት ያሉ ሲሆን በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ ስራ በመሆኑ በየብሎኩ ያሉ ስራ ፈላጊዎችን ከመለየት ጀምሮ እስከ ስልጠና ማመቻቸትና ስራ ማስያዝ ድረስ ጠንክረን በመስራት "በሀሳብ ልዕልና ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና" ልንሻገር ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ህዳር 12/2017
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 11 የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአባላት መረጃ